የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች በሚዛን የትራክተር መገጣጠሚያ ፋብሪካ አጀማመር ተዘዋውረው ጎበኙ።
የሚዛን አማን ከተማ ዋና ከንቲባ አቶ ግሩም ተማም የተመራው የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች የሚዛን ትራክተር ፋብሪካን የስራ እንቅስቃሴ ምልከታ አድርገዋል።
ከፍተኛ አመራሮቹ ሚዛን ትራክተር ፋብሪካ በፍጥነት ወደ ስራ በመግባት ፋብሪካው የሚገነባበትን ቦታ ለማስተካከልና ሼድ ለመገንባት እያደረገ ያለውን ጥረት አድንቀዋል።
በጉብኝቱም የከተማ አስተዳደሩ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ በላቸው ጎንደርና በፓርቲው የርእዮተ ዓለም ዘርፍ ሃላፊ አቶ ምትኩ ጢሞቲዮስ ተገኝተዋል።