መንግስት የአምራች ኢንዱስትሪውን ዘርፍ ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ በቁርጠኝነት በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ (አቶ ሀሰን መሀመድ)
image

መንግስት የአምራች ኢንዱስትሪውን ዘርፍ ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ በቁርጠኝነት በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ (አቶ ሀሰን መሀመድ)
======================================
ታህሳስ 21/2017 ዓ.ም (ኢሚ) በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና ግብርና ሚኒስቴር አስተባባሪነት ለእንስሳት የተመጣጠነ መኖ ለማቅረብ የሚያስችል የሀገር ውስጥ ማሽን አምራቾችን ከአስመራቾች ጋር ማስተሳሰር የሚያስችል የፊርማ ስምምነት ተካሄደ ።
መንግስት የአምራች ኢንዱስትሪውን ዘርፍ ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ በቁርጠኝነት በመስራት ላይ ይገኛል ያሉት የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሀሰን መሀመድ የተጀመረው ኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የአምራች ኢንዱስትሪውን ማነቆዎች በመፍታት ለዘርፉ ዘላቂ ልማትና ተወዳዳሪነት ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር መሆኑን ተናግረዋል ፡፡
የሀገር ውስጥ ማሽነሪዎችን በመጠቀም ለእንስሳት የተመጣጠነ መኖን ተደራሽ በማድረግ የሌማት ትሩፋት ንቅናቄን ውጤታማነት ለማረጋገጥ በቀጣይም ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በመሆን የተለያዩ ስራዎችን የምናከናውን ይሆናል ብለዋል፡፡
በዘርፉ የሚታዩ ዘርፈ ብዙ ችግሮችን ለይቶ ለመፍታት እንዲያስችል የማሽነሪ ኢንዱስትሪ ልማት ስትራቴጂ ሰነድ ዝግጅት በመጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ ያነሱት ሚኒስትር ዴኤታው ተጠናቆ ተግባራዊ ሲደረግ የዘርፉን ተወዳዳሪነት ወደላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግር ገልፀዋል፡፡
የመኖ ማቀነባበሪያና ሌሎች የግብርና ማሽነሪዎችን በሀገር ውስጥ ለማምረት የኢንዱስትሪ ሚኒስቴርና የግብርና ሚኒስቴር በጋራ በመሆን በርካታ ስራዎች በመስራት ላይ መሆኑን በመጠቀስ ከዚህ ቀደም በትግራይና በሲዳማ ክልሎች የተጀመሩትና የመኖ ማሽን አምራቾችን ከመኖ አቀናባሪዎች ጋር የማስተሳሰር ስራ መሰራቱንና ዛሬም የተከናወነው ስምምነት ከሶስት ክልሎች የቀረቡ ዘጠኝ የመኖ ማቀነባበሪያ ማሽነሪ ፍላጎቶችን መሰረት በማድረግ አምራቾችን ከአስመራቾች ጋር እርስበርስ ማስተሳሰር ዋና ዓለማው እንደሆነ አስረድተዋል፡፡
በቀጣይ ማሽነሪዎቹ ለመኖ አቀነባባሪዎቹ በተገባው ውል መሰረት በጥራት መቅረብ እንዲችል ቴክኒካል ድጋፎችን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያደርጋል ያሉት አቶ ሀሰን መሀመድ ለኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግሩ ዘርፉ የበኩሉን አስተዋፅኦ እንዲያደርግ ለማስቻል በትኩረት መስራት የሁሉም ድርሻ መሆኑን አሳስበዋል፡፡