"ጭኮ ሬስቶራንት" - የከፈተችው ኢትዮጵያዊት
#Ethiopia | በአዲስ አበባ ከተማ መገናኛ አካባቢ በልዮ ዲዛይን እና አገልግሎት የተለየው ጭኮ ሬስቶራንት እና ኬኮች የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር ምግቦችን እያዘጋጀ ለደንበኞቹ እያቀረበ መሆኑን ከ15 አመታት በላይ በውጭ ሀገር ሰርታ ሬስቱራንት የከፈተችው የድርጅቱ መስራች እና ዋና ባለቤት ወይዘሮ ወ/ሮ ስብለወንጌል ደበበ ለመገናኛ ብዙሃን ተቋማት በሰጠችው መግለጫ ገልጻለች።
ከ60 በላይ ለሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን በቋሚነት እና በጊዚያዊነት የስራ እድል የፈጠረው ጭኮ ሬስቶራንት እና ኬኮች በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ ሲገባ ከሁለት መቶ በላይ ለሚሆኑ ሰራተኞችን የስራ እድል እንደሚፈጥር በጋዜጣዊው መግለጫ መርሐግብሩ ላይ ተገልጿል።
ሁሉንም የእድሜ ክልል ታሳቢ በማድረግ የተገነባው እና አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኘው ጭኮ ሬስቱራንት እና ኬኮች በሀገራችንና በከተማችን ዕድገት ላይ የበኩሉን አስተዋፅኦ ለማድረግ የተቋቋመው ሲሆን ከውጭ የሚመጡ እንግዶችን ታሳቢ በማድረግ የቱሪዝም እንቅስቃሴው እንዲዳብር ጉልህ ሚና በመጫወት ላይ እንደሚገኝ በሆቴል ሙያ ዘርፍ ከፍተኛ ልምድ ያላቸው የጭኮ ሬስቱራንት እና ኬኮች ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አንተነህ አለሙ በመግለጫው ላይ ገልጸዋል።
« ጭኮ» በሚል ሀገረኛ ስያሜ የተሰየመው ሬስቱራንት ከሚሰጠው የምግብ እና የመጠጥ አገልግሎት ባሻገር ዘወትር በየሳምንቱ ቅዳሜ ከቀኑ 11:30 ጀምሮ እስከ ምሽት 3:00 ድረስ እንኮይ የሙዚቃ ባንድ ቀየት ያሉ እና ዘመናዊ ሙዚቃዎችን በቀጥታ ከመድረክ በእውቅ ድምጻዊያን ለቤቱ ደንበኞች ያቀርባል።
ጭኮ ሬስቱራንት እና ኬኮች ብራንዱን ከፍ በማድረግ አዲስ አበባ ከተማ ላይ ተጨማሪ ቅርንጫፎችን ለመክፈት በእቅድ ላይ የሚገኝ መሆኑን ገልጿል።